Date of death22.Feb.2024
LocationEthiopia

Damte Asegidew

ዳምጤ አሰግደው

Damte Asegidew
Source

Amhara Association of America View →

Damte Asegidew was a 40-year-old farmer and father of four. He lived in Yenagnet Kebele, in the Dejen district of the Amhara region, and was well respected in his community. He was known for his hard work.

On 22 February, Damte was with a group of villagers doing some construction work on a hall meant for funeral services at the local church, St George’s. At around 3.30pm, a group of Ethiopian National Defense Force soldiers appeared and began firing on the villagers, accusing them of helping Fano militia forces to construct a fort. Damte was shot in the head, and died at the scene. At least 20 other civilians were injured in the attack.

ዳምጤ አሰግደው የ40 ዓመት አርሶ አደር እና የአራት ልጆች አባት ነበር። በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን፣ በደጀን ወረዳ፣ የናኛት ቀበሌ ነዋሪ የነበረ ሲሆን፣ በስራው ታታሪነት የሚታወቅ እና በማኅበረሰቡ ዘንድም የተከበረ ሰው ነበር።

የካቲት 14 ቀን፣ ዳምጤ ከሌሎች የአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በመሆን፣ በአካባቢው በሚገኘው በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ፍታት አገልግሎት የሚውል አዳራሽ ግንባታ ስራ ላይ እየተሳተፈ ነበር። ከቀኑ 9:30 ሰዓት ገደማ፣ የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ወታደሮች በድንገት በቦታው በመገኘት በግንባታ ስራ ላይ የነበሩትን የአካባቢው ነዋሪዎች ለፋኖ ሚሊሻ ኃይሎች ምሽግ እየቆፈራችሁ ነው በሚል የእሩንታ ተኩስ ከፈቱ። በዚህም ዳምጤ ጭንቅላቱ ላይ በጥይት ተመቶ ወዲያውኑ ህይወቱ ያለፈ ሲሆን፣ በዚሁ ጥቃት ከ20 ያላነሱ ሌሎች ንጹሃን ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል።